በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የተማሪ ተኮር የክፍል ውስጥ አተገባበር ፍተሻ፤ በአሥረኛ ክፍል ተተኳሪነት አማርኛን ለማስተማር ሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት

Show simple item record

dc.contributor.author ኃይላይ ተስፋዬ (ዶ/ር)
dc.date.accessioned 2025-11-05T06:36:47Z
dc.date.available 2025-11-05T06:36:47Z
dc.date.issued 2015-02
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/2824
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና አላማ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በዳውሮ ዞን በማረቃ ወረዳ ጎዞ ባሙሽ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የተማሪ ተኮር የክፍል ውስጥ አተገባበር መፈተሽ ነው፡፡ ጥናቱ ሦስት መሰረታዊ ጥያቄዎች ሲኖሩት እነርሱም የተማሪ ተኮር ማስተማሪያ በክፍል ውስጥ ሲተገብር የተሰጠው ትኩርት ምን ይመስላል፤ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የተማሪ-ተኮር የክፍል ውስጥ አተገባበር ጠንካራና ደካማ ጎኖች ምን ምን ናቸው? እና አማርኛን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚያስተምሩ መምህራን የተማሪ-ተኮር አተገባበርን በክፍል ውስጥ ሲተገበር የመምህሩ እና የተማሪው ተግባራት ምን ምን ነበሩ? የሚሉት ናቸው፡፡ ጥናቱ ገላጭ የምርምር ዘዴን የተከተለ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ጥናቱን ከግብ ለማድረስ የመረጃ መሰብሰቢያ ሆነው ያገለገሉ መሳሪያዎች ቃለ መጠይቅና ምልከታ ናቸው፡፡ መረጃዎቹም በክለሳ ድርሳን ላይ የሰፈሩ ንድፈ ሃሳባዊ ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ አይነታዊ የአተናተን ዘዴን በመጠቀም ተተንትነዋል፡፡ በመረጃዎቹ የተገኘው ውጤት እንደሚያመለክተው በተተኳሪው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የተማሪ ተኮር የክፍል ውስጥ አተገባበራቸው የተማሪውን ችሎታ ያገናዘበ መሆኑ በጠንካራ ጎን የሚነሳ ቢሆንም በተወሰነ መልኩ ክፍተቶች የታየባቸው መሆኑ ደግሞ በደካማ ጎን ሊነሳ የሚችል ነው፡፡ ስለዚህ ወደፊት በአተገባበሩ ተገቢውን ትኩረት መስጠት እንደሚገባቸው ይጠቁማል፡ en_US
dc.title በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የተማሪ ተኮር የክፍል ውስጥ አተገባበር ፍተሻ፤ በአሥረኛ ክፍል ተተኳሪነት አማርኛን ለማስተማር ሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search AMU IR


Advanced Search

Browse

My Account