Abstract:
የዚህ ጥናት ዋና አላማ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በዳውሮ ዞን በማረቃ ወረዳ ጎዞ ባሙሽ 2ኛ ደረጃ
ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የተማሪ ተኮር የክፍል ውስጥ አተገባበር መፈተሽ
ነው፡፡ ጥናቱ ሦስት መሰረታዊ ጥያቄዎች ሲኖሩት እነርሱም የተማሪ ተኮር ማስተማሪያ በክፍል ውስጥ
ሲተገብር የተሰጠው ትኩርት ምን ይመስላል፤ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የተማሪ-ተኮር የክፍል ውስጥ
አተገባበር ጠንካራና ደካማ ጎኖች ምን ምን ናቸው? እና አማርኛን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ
የሚያስተምሩ መምህራን የተማሪ-ተኮር አተገባበርን በክፍል ውስጥ ሲተገበር የመምህሩ እና የተማሪው
ተግባራት ምን ምን ነበሩ? የሚሉት ናቸው፡፡ ጥናቱ ገላጭ የምርምር ዘዴን የተከተለ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት
ጥናቱን ከግብ ለማድረስ የመረጃ መሰብሰቢያ ሆነው ያገለገሉ መሳሪያዎች ቃለ መጠይቅና ምልከታ ናቸው፡፡
መረጃዎቹም በክለሳ ድርሳን ላይ የሰፈሩ ንድፈ ሃሳባዊ ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ አይነታዊ
የአተናተን ዘዴን በመጠቀም ተተንትነዋል፡፡ በመረጃዎቹ የተገኘው ውጤት እንደሚያመለክተው በተተኳሪው
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የተማሪ ተኮር የክፍል ውስጥ አተገባበራቸው የተማሪውን ችሎታ ያገናዘበ
መሆኑ በጠንካራ ጎን የሚነሳ ቢሆንም በተወሰነ መልኩ ክፍተቶች የታየባቸው መሆኑ ደግሞ በደካማ ጎን
ሊነሳ የሚችል ነው፡፡ ስለዚህ ወደፊት በአተገባበሩ ተገቢውን ትኩረት መስጠት እንደሚገባቸው ይጠቁማል፡