Abstract:
የዚህ ጥናት ዋና አላማ የአማርኛ ኢ-አፍ ፈት ተማሪዎች አማርኛ ቋንቋን ሲማሩ ያላቸው
ፍላጎት እና የውጤት ተዛምዶ መካካል ያለውን ልዩነት መፈተሽ ነው። ጥናቱ ገላጭ
ተዛምዷዊ ንድፍ የተከተለ ነው። በአይነቱ መጠናዊ የምርምር ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደውም
በበዴሳ ሁለተኛ ደረጃ በ2014 ዓ.ም በሚማሩ የአማርኛ ኢ-አፍ ፈት አስረኛ ክፍል 80
ተማሪዎች ላይ ነው፡፡ ትምህርት ቤቱ በአመቺ ናሙና የተመረጠ ሲሆን ተማሪዎቹ ደግሞ
በእጣ ናሙና ስልት ተመርጠዋል፡፡ በፈተና እና በጽሁፍ መጠይቅ አማካኝነት ከተሰባሰቡ
በኃላ የተሰበሰቡት መረጃዎችም በነጠላ ናሙና ቲ-ቴስት እና በፒርሰን ተዛምዶ መወሰኛ
ቀመር መረጃ በመተንተኛ ዘዴ ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ የትንተናው ውጤትም በተማሪዎች
የመማር ፍላጎት እና በውጤት መካከል ያለው ተዛምዶ (-.241) መሆኑን አረጋግጧል፡፡
ይህም የተዛምዷቸው መጠን ሲታይ (r= 0.20-0.39 ያለው፣ 2009 ዓ.ም፡ 340)
እንደሚገልጹት በዝቅተኛ ተዛምዶ ስር ይፈረጃል፡፡ ይህም በተማሪዎች አማርኛ ቋንቋን
የመማር ፍላጎትና የትምህርት ውጤት መካከል ጉልህ የሆነ ዝቅተኛ አሉታዊ ተዛምዶ ያለ
መሆኑን እና በተማሪዎች መማር ውስጥ የመማር ፍላጎትና የትምህርት ውጤት ተነጣጥለው
የማይታዩ ተላውጦዎች መሆናቸው አመላክቷል