አዕምሯዊ የመማር ብልሃቶች የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት የማሳደግ ሚና፤ በሰባተኛ ክፍል ዐማርኛ ኢአፍፈት ተማሪዎች ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author ዶ/ር ኃይላይ ተስፋይ
dc.date.accessioned 2019-11-12T06:53:17Z
dc.date.available 2019-11-12T06:53:17Z
dc.date.issued 201-03
dc.identifier.uri http://hdl.handle.net/123456789/1240
dc.description.abstract አህጽሮተጥናት (Abstract) የጥናቱ ዋና ዓላማ አዕምሯዊ የመማር ብልሃቶች የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት የማሳደግ ሚና መፈተሽ ነው፡፡ ዓላማውን ለማሳካትም ፍትነትመሰል የጥናት ንድፍ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ በመሆኑም አዕምሯዊ ብልሃቶች በይዘትነትና በትግበራ የሚማሩ የብልሃት ቡድን፣ አዕምሯዊ ብልሃቶችን በተለያዩ መልመጃዎች በትግበራ የሚማሩ የብልሃትአልባ ቡድንና በተለመደው የማንበብ ትምህርት አቀራረብ የሚማረው የቁጥጥር ቡድን የአንብቦ መረዳት ትምህርትን በ4 ሳምንታት ለ20 ክፍለጊዜያት እንዲማሩ ተደርጓል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎችም በደቡብ ክልል፣ በወላይታ ዞን፣ በሶዶ ከተማ በጊዮርጊስ ትምህርት ቤት በ2011 ዓ.ም በመማር ላይ ከሚገኙ ስድስት የሰባተኛ ክፍል መማሪያ ክፍሎች ውስጥ በብዛት ኢአፈፈት የሚገኙባቸው ሦስት መማሪያ ክፍሎች ተመርጠዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ በብልሃት 42፣ በብልሃትአልባ ቡድኑ 38፣ በቁጥጥር ቡድኑ 38 በጥቅሉ 118 ተማሪዎች ናቸው፡፡ ከተሳታፊዎቹም ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተናና የማንበብ ተነሳሽነት የፅሁፍ መጠይቆች አማካይነት መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ መረጃዎቹም በአማካይ ውጤት፣ በመደበኛ ልይይት፣ በባለሁለት ተላውጦ ልይይትና በባዕድ ናሙና ቲ-ቴስት ተሰልተው ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ግኝቶች እንዳመላከቱትም በብልሃትና በብልሃት አልባ ሁለት አቀራረቦች የተማሩት በተለመደው የማንበብ ትምህርት ከተማሩት ይልቅ በአንብቦ መረዳት ችሎታቸው ጉልህ መሻሻል አሳይተዋል፡፡ ይሁን እንጂ በማንበብ ተነሳሽነት ላይ ጉልህ ሚና አላሳየም፡፡ እንዲሁም በብልሃትና በብልሃት አልባው ቡድን መካከልም የአንብቦ መረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ጉልህ ልዩነት እንደሌለው አሳይቷል፡፡ ይህም ከሁለቱ የብልሃት አቀራረቦች አዕምሯዊ ብልሃትን በይዘትነትና በትግበራ መማርና በትግበራ ብቻ መማር ልዩነት እንደሌለው ያሳያል፡፡ ስለዚህ ትግበራው በሁለቱም ቡድኖች ስለሚገኝ በይዘትነት ከመማር ይልቅ በትግበራ መማር አስተዋፅኦ እንዳለው ያመለክታል፡፡ ከጥናቱ ግኝቶችም በመነሳት አስተያየቶች ተሰጥተዋል፤ የወደፊት የምርምር ጥቆማዎችም ተመላክተዋል፡፡ en_US
dc.description.sponsorship አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ en_US
dc.publisher አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ en_US
dc.title አዕምሯዊ የመማር ብልሃቶች የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት የማሳደግ ሚና፤ በሰባተኛ ክፍል ዐማርኛ ኢአፍፈት ተማሪዎች ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search AMU IR


Advanced Search

Browse

My Account